የተሻለ ምድጃ፣ የተሻለ ኑሮ የእኛ መፍትሄዎች ንጹህ፣ ጤናማ እና ቆጣቢ የማብሰያ መንገድ ይምረጡ። የአነጋ ምድጃዎች ነዳጅን በቁጠባ እንዲጠቀሙ፣ ጭስን እንዲቀንሱ እና ለመጠቀም ቀላል እንዲሆኑ ተዘጋጅተዋል። ለፍላጎትዎ የሚስማማውን የአነጋ ምድጃ ይምረጡ። ዘላቂ እና ለአካባቢ ተስማሚ የግሪንሃውስ ጋዝ ልቀትን ይቀንሳል የቤት ውስጥ አየር ጥራትን ያሻሽላል አነጋን ለምን ይምረጡ? ኃይልና ነዳጅን በቁጠባ ይጠቀማል ጤናማ ማብሰያ ለአጠቃቀም የተመቸ በኢትዮጵያ የተመረተ ዋስትናና ከሽያጭ በኋላ አገልግሎት ያለው ለኢትዮጵያ ምግብ አሰራር የተመቸ እስካሁን የደረስንበት 0 በዓመት ወደ ነዳጅ የሚለወጥ የባዮማስ ቆሻሻ (ቶን) 0 ጤናቸው የተሻሻለ ቤተሰቦች 0 በዓመት የሚቀንስ የCO₂ ልቀት (ቶን) 0 በባዮቻር መልክ በአፈር ውስጥ የሚታሰር ካርቦን (ቶን/በዓመት) የተሻሻለ፦ ነሐሴ 2018 ምርቶቻችን አነጋ ማን ነው? ኢትዮጵያ ወደ ንጹህ የማብሰያ መንገዶች አለመሸጋገሯ በጤና፣ በአካባቢ፣ በአየር ንብረት እና በሴቶች ላይ በሚያሳድረው ጉዳት ምክንያት በየዓመቱ 157 ቢሊዮን ዶላር ያህል እንደምታጣ ይገመታል። አነጋ ይህን ችግር ለመቀነስ የተለያዩ የማብሰያ ቴክኖሎጂዎችን የሚነድፍና የሚያመርት ማህበራዊ ዓላማ ያለው ድርጅት ነው። ምርቶቻችን ከቀላል ተገጣጣሚ የእንጨት ምድጃዎች፣ የከሰል ምድጃዎችና የኤሌክትሪክ ምድጃዎች እስከ ፋን የሚጠቀሙ ንጹህ የቤትና የተቋማት ምድጃዎች ድረስ ይደርሳሉ። የፋን ምድጃዎቻችን የነዳጅ እንክብሎችን ይጠቀማሉ። እነዚህንም እንክብሎች እንደ የእንጨት ትቢያ፣ የቡና ቅሪት፣ የጫት ግንድ እና የቡና ቅርፊት ካሉ የባዮማስ ቆሻሻዎች እናመርታለን። ስለ አነጋ የበለጠ ይወቁ አጋሮቻችን የነዳጅ እንክብሎቻችን የነዳጅ እንክብሎቻችንን እንደ የእንጨት ትቢያ፣ የቡና ቅሪት፣ የጫት ግንድ እና የቡና ቅርፊት ካሉ የባዮማስ ቆሻሻዎች እናመርታለን። እንደ ጥሬ እቃው ዓይነት በሰዓት ከ500 እስከ 1000 ኪሎ ግራም የማምረት አቅም አለን። እንክብሎቹ መጠናቸው አንድ ዓይነት ነው፣ እርጥበታቸው ዝቅተኛ ነው፣ በትንሽ መጠን ከፍተኛ ኃይል ይይዛሉ፣ ለማጓጓዝና ለማከማቸትም ቀላል ናቸው። በዚህም ምክንያት ለጋዝፋየር ምድጃዎች ከሌሎች ጠጣር የባዮማስ ነዳጆች የተሻሉ ናቸው። በፋን በሚሰሩ የቤት ጋዝፋየር ምድጃዎቻችን ውስጥ ከተቃጠሉ በኋላ ባዮቻር (ከሰል) ይቀራል። ይህንን ባዮቻር ከደንበኞቻችን መልሰን ገዝተን ለውሃና ለአየር ማጣሪያ እንዲሁም ለአፈር ማሻሻያ እንጠቀምበታለን። እንዴት እንደሚሰራ የበለጠ ይወቁ አሁን ይዘዙ የማብሰያ መንገድዎን ያሻሽሉ። አነጋ ቆጣቢ፣ ንጹህ እና ለመጠቀም ቀላል የሆኑ የፔሌት፣ የከሰል እና የኤሌክትሪክ ምድጃዎችን ያመርታል። ለቤትዎና ለአኗኗርዎ የሚስማማውን ምድጃ ይምረጡ። ዛሬውኑ ይዘዙ። ምርቶቻችንን ይመልከቱ ያግኙን